ለድህረምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች
ለድህረምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2019 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የትምህርት ዘርፎች በመደበኛ እና በሳምንት መጨረሻ የስልጠና መርሃ ግብሮች የመግቢያ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾችን ተቀብሎ በሁለተኛ ድግሪ ማስተማር ይፈልጋል።
Program | Enrollment Type | Departments |
Postgraduate | Regular | MPH in Epidemiology |
MPH in Health Service Management | ||
MPH in Monitoring & Evaluation | ||
MPH in Public Health Nutrition | ||
MSc in Integrated Clinical and Community Mental Health | ||
MSc in Medical Microbiology | ||
Weekend | MPH in Epidemiology | |
MPH in Health Service Management | ||
MPH in Monitoring & Evaluation | ||
MPH in Public Health Nutrition |
የመመዝገቢያ መስፈርቶች፤
ከስልጠና መስኩ ጋር ተዛማጅ የሆነ በጤና የትምህርት ዘርፎች የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው እና የትምህርት ማስረጃ (Original Degree & Student Copy) ማቅረብ የሚችሉ::
በትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጠውን National Graduate Admission Test (NGAT) ፈተና ተፈተነው ያለፉ መሆናቸውን የሚያሳይ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ::
የድጋፍ ደብዳቤ /Recommendation Letter/ ከመ/ቤት ኃላፊ ወይም ከቀድሞ መምህር የተጻፈ ማቅረብ የሚችሉ::
አመልካቾች ማቅረብ የሚጠበቅባቸው መረጃዎች፡
ሙሉ የትምህርት ማስረጃ፡ የ8ኛ፣ 10ኛ፣ 12ኛ ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት እንዲሁም ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፤ድግሪ፤ ስቱደንት ኮፒ፤ ከዚህ በፊት የመጀመሪያ ድግሪ የተማሩት በዲፕሎማ ከሆነ የዲፕሎማ ስቱደንት ኮፒ እና ዲፕሎማ ማምጣት ይኖርባችኋል::
ፎቶግራፍ፡ የፓስፖርት መጠን ወይም (3x4) ፎቶግራፍ::
የድጋፍ ደብዳቤ፡ የድጋፍ ደብዳቤ /Recommendation Letter/ ከመ/ቤት ኃላፊ ወይም ከቀድሞ መምህር የተጻፈ::
የመመዝገቢያ ክፍያ፡ የመመዝገቢያ ክፍያ 300 ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000488221257 ገቢ በማድረግ የክፍያ ደረሰኝ ::
ስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ፡ በመንግሥት /በድርጅት ስፖንሰርነት ለመማር ለሚያመለክቱ አመልካቾች በመሥሪያ ቤቱ ወይም በድርጅቱ ኃላፊ የተፈረመ ስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ::
አግባብነት ያለው የስራ ልምድ (Work Experience) ፡ አመልካቾች ከሚሰሩበት ተቋም እንዲሁም የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አመልካቾች የድጋፍ ደብዳቤ ከቢሮው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የፈተና መስጫ፣ የውጤት ማሳወቂያ፣ የምዝገባ ጊዜ እና ቦታ
የማመልከቻ ጊዜና ቦታ፡ ከነሀሴ 27- ጳጉሜ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት፤ የምዝገባ ቦታ በዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ በዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሬጅስትራር ይሆናል፡፡
ለፈተና ያለፉ አመልካቾች ዝርዝር የሚገለጽበት ቀን፡ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም::
የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀንና ቦታ: የመግቢያ ፈተና በኮሌጁ ግቢ የሚስጥ ሲሆን የፈተና ቀኑን በውስጥ ማስታወቂያ በኮሌጁ ሬጅስትራር የማስታወቂያ ሠሌዳ ላይ ከፈተና ቀን በፊት የሚለጠፍ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም በኮሌጁ የማህበራዊ ሚዲያዎች መከታተል ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡
የ8ኛ፡10ኛ ክፍል ወይም 12ኛ ክፍል የጨረሱበት ሰርተፊኬት እና ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘው ዲፕሎማ ከሆነ ዲፕሎማው በተገኘበት ክልል የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ወይም የዞን/የከተማ መስተዳደር የሥራና ስልጠና ቢሮ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ እንዲሁም የደረጃ 4 ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት (COC) ማረጋገጥ (Authentication) ይኖርባቸዋል።
ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተመረቁ በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የትምህርት ማስረጃቸውን ማረጋገጥ (Authentication) ይኖርባቸዋል።
የመግቢያ ፈተናውን ያለፉ አመልካቾች በምዝገባ ወቅት ዋናውን የትምህርት ማስረጃ ከማይመለስ ሁለት ኮፒ፣ ሁለት ጉርድ ፎቶ፣ እና የማመልከቻ ከፍያ ደረሰኝ ይዘው መቅረብ አለባቸው።
የመግቢያ ፈተና ያለፉ አመልካቾች ኦፊሻል ትራንስክሪፕት /Official Transcript/ በኮሌጁ በፖስታ ሳጥን ቁጥር 3268 በኩል ከምዝገባ ቀን ጀምሮ ባለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
የስፖንሶርሺፕ ቅፅ ከኮሌጁ ሬጂስትራር ማግኘት ትችላላችሁ።
የተሟላ መረጃ ያላቀረቡ አመልካቾችን የማንቀበል በመሆኑ ማመልከቻውን በጥንቃቄ እንዲያሟሉ እንመክራለን፡፡
